\v 3 ከነገርኋችሁ ቃል የተነሣ እናንተ ንጹሓን ናችሁ። \v 4 በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ላይ ካልኖረ በቀር በራሱ ፍሬ ማፍራት እንደማይችል ሁሉ፣ እናንተም በእኔ ካልኖራችሁ ፍሬ ማፍራት አትችሉም።