am_jhn_text_ulb/14/28.txt

1 line
819 B
Plaintext

\v 28 'እሄዳለሁ፣ ዳግመኛም ወደ እናንተ እመጣለሁ' ብዬ የነገርኋችሁን ቃል ሰምታችኋል። ከወደዳችሁኝስ ወደ አብ በመሄዴ ደስ ሊላችሁ ይገባ ነበር፤ ምክንያቱም አብ ከእኔ ይበልጣል። \v 29 ይህ ነገር በሚፈጸምበት ጊዜ ታምኑ ዘንድ አሁን ከመሆኑ በፊት አስቀድሜ ነገርኋችሁ። \v 30 የዚህ ዓለም ገዢ ስለሚመጣ፣ ከእናንተ ጋር ብዙ አልነጋገርም። እርሱ በእኔ ላይ ኀይል የለውም። \v 31 ነገር ግን እኔ አብን እንደምወድ ዓለም እንዲያውቅ ልክ እርሱ ትእዛዝ እንደ ሰጠኝ፣ አብ የሚያዘኝን አደርጋለሁ። ተነሡ ከዚህ እንሂድ።»