am_jhn_text_ulb/14/15.txt

1 line
509 B
Plaintext

\v 15 የምትወዱኝ ከሆነ ትእዛዜን ትጠብቃላችሁ። \v 16 እኔም ለዘላለም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ እንዲሰጣችሁ አብን እለምናለሁ። \v 17 እርሱም የእውነት መንፈስ ነው፤ ዓለም ስለማያየው ወይም ስለማያውቀው አይቀበለውም። ይሁን እንጂ፣ ከእናንተ ጋር ስለሚኖርና በውስጣችሁም ስለሚሆን፣ እናንተ ታውቁታላችሁ።