am_jhn_text_ulb/14/04.txt

1 line
629 B
Plaintext

\v 4 ወዴት እንደምሄድ መንገዱን ታውቃላችሁ።» \v 5 ቶማስ ኢየሱስን፣ «ጌታ ሆይ፣ ወዴት እንደምትሄድ አናውቅም፣ መንገዱን እንዴት ማወቅ እንችላለን?» በማለት ጠየቀው። \v 6 ኢየሱስ እንዲህ አለው፤ «እኔ መንገድ፣ እውነትና ሕይወት ነኝ፤ በእኔ ካልሆነ በቀር ማንም ሰው ወደ አብ ሊመጣ አይችልም። \v 7 እኔን ብታውቁኝ ኖሮ አባቴንም ባወቃችሁት ነበር። ከአሁን ጀምሮ ታውቁታላችሁ አይታችሁትማል።»