am_jhn_text_ulb/06/10.txt

1 line
672 B
Plaintext

\v 10 ኢየሱስ፣ ‹‹ሕዝቡ እንዲቀመጡ አድርጉ›› አላቸው፡፡ ስፍራውም በሣር የተሸፈነ ነበር፡፡ ስለዚህ ቍጥራቸው አምስት ሺህ የሚያህል ወንዶች ተቀመጡ፡፡ \v 11 ከዚያም ኢየሱስ እንጀራውንና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ባረከና ለተቀመጡት ዐደለ፡፡ በተመሳሳይ መንገድ ከዓሣውም የሚፈልጉትን ያህል ዐደላቸው፡፡ \v 12 ሕዝቡ በጠገቡ ጊዜ፣ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፣ ‹‹አንዳችም እንዳይጣል የተረፈውን ፍርፋሪ ሰብስቡ›› አላቸው፡፡