\v 43 እኔ በአባቴ ስም መጥቼ አልተቀበላችሁኝም፤ ሌላው በራሱ ስም ቢመጣ ግን ትቀበሉታላችሁ። \v 44 እናንተ አንዳችሁ ከሌላችሁ ክብር የምትቀበሉ፣ ነገር ግን ከአንዱ አምላክ የሚመጣውን ክብር የማትሹ ከሆነ፣ እንዴት ልታምኑ ትችላላችሁ?