am_jhn_text_ulb/05/36.txt

1 line
515 B
Plaintext

\v 36 እኔ ያለኝ ምስክርነት ግን ከዮሐንስ ምስክርነት ይበልጣል፡፡ አብ እንድፈጽመው የሰጠኝ፣ እኔም እየሠራሁት ያለሁት ሥራ አብ እንደ ላከኝ ይመሰክራል። \v 37 የላከኝ አብ እርሱ ስለ እኔ መስክሮአል፤ እናንተም ከቶ ድምፁን አልሰማችሁም፤ መልኩንም አላያችሁም፤ \v 38 እርሱ በላከው አላመናችሁምና ቃሉ በእናንተ አይኖርም።