am_jhn_text_ulb/21/22.txt

1 line
518 B
Plaintext

\v 22 ኢየሱስ፣ «እኔ እስክመጣ እንዲቆይ ብፈልግስ አንተን ምን ይመለከትሃል? ዝም ብለህ ተከተለኝ» አለው። \v 23 በዚህ ምክንያት «ያ ደቀ መዝሙር አይሞትም» የሚል ወሬ በየ ስፍራው ተሠራጨ። ኢየሱስ ግን ለጴጥሮስ፣ «እኔ እስክመጣ እንዲቆይ ብፈልግስ አንተን ምን ይመለከትሃል?» አለው እንጂ ያ ደቀ መዝሙር አይሞትም አላለውም።