am_jhn_text_ulb/21/17.txt

1 line
839 B
Plaintext

\v 17 ለሦስተኛ ጊዜ፣ «የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፣ ትወደኛለህ?» አለው። ለሦስተኛ ጊዜ «ትወደኛለህ ወይ?» ብሎ ስለ ጠየቀው ጴጥሮስ በጣም ዐዘነ። ቀጥሎም፣ «ጌታ ሆይ፣ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንደምወድህም ታውቃለህ» አለው። ኢየሱስም «በጎቼን መግብ። \v 18 እውነት፣ እውነት እልሃለሁ፣ ወጣት እያለህ ልብስህን ራስህ ለብሰህ ወደምትፈልገው ቦታ ትሄድ ነበር፤ ስታረጅ ግን ሌላ ሰው ልብስህን አልብሶህ ወደማትፈልገው ቦታ ይወስድሃል፣ በዚያን ጊዜ አንተ እጅህን ከመዘርጋት ውጪ ሌላ ማድረግ የምትችለው ነገር አይኖርም» አለው።