am_jhn_text_ulb/21/01.txt

1 line
817 B
Plaintext

\c 21 \v 1 እነዚህ ነገሮች ከተፈጸሙ በኋላ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንደ ገና በጥብርያዶስ ባሕር አጠገብ ተገለጠላቸው፤ ሁኔታውም እንደዚህ ነበር፦ \v 2 ስምዖን ጴጥሮስ ዲዲሞስ ከተባለው ከቶማስ፣ ከገሊላ አውራጃ ከቃና መንደር ከሆነው ከናትናኤል፣ ከዘብዴዎስ ልጆችና ከሌሎች ሁለት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ጋር ዐብረው ነበሩ። \v 3 ስምዖን ጴጥሮስ፣ «ዓሣ ለማጥመድ መሄዴ ነው» አላቸው። እነርሱም፣ «እኛም ከአንተ ጋር እንሄዳለን» አሉት። በጀልባ ተሳፍረው ሄዱ፤ ነገር ግን በዚያች ሌሊት ምንም ዐሣ አላጠመዱም።