am_jhn_text_ulb/17/06.txt

1 line
528 B
Plaintext

\v 6 ከዓለም ለሰጠኸኝ ለእነዚህ ሰዎች ስምህን ገለጥሁላቸው። የአንተ ነበሩ፣ ለእኔም ሰጠሃቸው፣ ቃልህንም ጠብቀዋል። \v 7 አሁን ከአንተ የተቀበልኋቸው ነገሮች ሁሉ በርግጥ ከአንተ እንደ መጡ አምነዋል፣ \v 8 የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና። እነርሱም ተቀብለውታል፤ ከአንተ እንደ መጣሁ አውቀዋል አንተ እንደላክኸኝም አምነዋል።