am_jhn_text_ulb/11/38.txt

1 line
612 B
Plaintext

\v 38 ከዚያም ኢየሱስ አሁንም በውስጡ እየቃተተ ወደ መቃብሩ ሄደ፡፡ መቃብሩ ዋሻ ነበረ፣ ድንጋይም ተገጥሞበት ነበር፡፡ \v 39 ኢየሱስ፣ “ድንጋዩን አንሡት” አለ፡፡ የሟቹ የአልዓዛር እኅት ማርታም ኢየሱስን፣ “ከሞተ አራት ቀን ስለሆነው፣ በአሁኑ ጊዜ ገላው ይበሰብሳል” አለችው፡፡ \v 40 ኢየሱስ ማርታን፣ “ብታምኚስ፣ የእግዚአብሔርን ክብር እንደምታዪ አልነገርሁሽምን” አላት፡፡