\v 25 ጻድቅ አባት ሆይ፣ ዓለም አላወቀህም፤ እኔ ግን አውቅሃለሁ፤ እነዚህም አንተ እንደ ላክኸኝ አውቀዋል፡፡ \v 26 አንተን እንዲያውቁ አድርጌአለሁ፤ እኔን የወደድህበት ፍቅር በእነርሱም እንዲሆንና እኔም በእነርሱ እንድሆን ስምህን አስታውቃቸዋለሁ፡፡