\v 21 ከዚያም ማርታ ኢየሱስን፣ “ጌታ ሆይ፣ አንተ እዚህ ብትኖር ኖሮ ወንድሜ ባልሞተም ነበር፡፡ \v 22 አሁንም ቢሆን የምትለምነውን ሁሉ እግዚአብሔር እንደሚሰጥህ ዐውቃለሁ” አለችው፡፡ \v 23 ኢየሱስ፣ “ወንድምሽ ይነሣል” አላት፡፡