am_jhn_text_ulb/17/09.txt

1 line
625 B
Plaintext
Raw Normal View History

\v 9 እነርሱ የአንተ ናቸውና አንተ ለሰጠኸኝ ለእነርሱ እንጂ ለዓለም አልጸልይም፡፡ \v 10 የእኔ የሆነው ሁሉ የአንተ ነው፤ የአንተ የሆነውም ነገር ሁሉ የእኔ ነው፤ እኔ በእነርሱ ከብሬአለሁ፡፡ \v 11 እኔ ወደ አንተ እመጣለሁና። ከእንግዲህ በዓለም አልኖርም፤ እነርሱ ግን በዓለም ውስጥ ናቸው፡፡ ቅዱስ አባት ሆይ፣ እኔና አንተ አንድ እንደ ሆንን አንድ እንዲሆኑ በሰጠኸኝ በስምህ ጠብቃቸው፡፡