am_jer_tn/25/34.txt

30 lines
2.7 KiB
Plaintext

[
{
"title": "እረኞች",
"body": "ያህዌ ስለ እስራኤል መሪዎች ለህዝቡ ሃላፊነት እንዳለባቸው እና አንደሚጠብቁት እረኞች አድርጎ እና በውስጠ ታዋቂነት እነርሱ በጎች እንደሆኑ ይናገራል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "በአፈር ላይ ተንከባለሉ",
"body": "ይህ የሀዘን፣ ለቅሶ ወይም ጭንቀት ምልክት ነው፡፡ (ምልክታዊ/ትምዕርታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "እናንተ የመንጋው ጠባቂዎች",
"body": "ይህም ሀረግ እንደዚሁ፣ ህዝቡን ለመጠበቅ ሃላፊነት ያለባቸውን እና እንደ በግ መንጋ የተገለጸውን ህዝብ የሚጠብቁትን የእስራኤልን መሪዎች ያመለክታል፡፡ \"እናንተ የእስራኤል መሪዎች\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የመታረጃችሁ ቀን ቀርቧል",
"body": "ብዙውን ጊዜ የሚታረዱት በጎች ናቸው፣ ነገር ግን እዚህ ስፍራ ያህዌ እረኞቹን አርዳለሁ ይላል፡፡ \"መታረድ\" የሚለው ቃል በግሳዊ ሀረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ \"እናንተን የማርድበት ጊዜ ደርሷል\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ምጸት እና ረቂቅ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እንደ ውብ ሸክላ ስትወድቁ ትበታተናላችሁ",
"body": "ያህዌ ስለ እስራኤል መሪዎች መጥፋት መሬት ላይ ወድቆ እንደ ደቀቀ የሸክላ ስብርባሪ አድርጎ ይናገራል፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ \"እንደ ውብ ሸክላ ትወድቃላችሁ የደቀቀ ስብርባሪያችሁ ምድር ላይ ይበታተናል\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ያህዌ መሰማሪያቸውን ይደመስሳል",
"body": "መሪዎቿ በሰላም እየኖርን ነው ብለው "
},
{
"title": "ያህዌ መሰማሪያቸውን ያጠፋል",
"body": "ያህዌ መሪዎቿ መንጋውን የሚንከባከቡበት \"መሰማሪያ\" መልካም እንደሆነ እና በሰላም እየኖሩ እንደሆነ ስለሚያስቡ መሪዎች ይናገራል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]