am_jer_tn/01/17.txt

34 lines
2.5 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አያያዥ ሀሳብ፡-",
"body": "እገዚአብሔር ለኤርምያስ መናገሩን ቀጥሏል፡፡ "
},
{
"title": "አትፍራቸው … በፊታቸው አስፈራሃለሁ",
"body": "እዚህ ላይ “አትፍራቸው” የሚለው ከመጠን በላይ መፍራትን ይወክላል፣ “አስፈራሃለሁ” የሚለው ደግሞ ኤርምያስን በጣም እንዲፈራ ማድረግን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አትፍራ … አስፈራሃለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እነሆ",
"body": "“ትኩረት ስጥ!”"
},
{
"title": "በምድሪቱ ሁሉ ላይ እንደ ተመሸገ ከተማ፣ እንደ ብረትም ዓምድ፣ እንደ ናስም ቅጥር ዛሬ አድርጌሃለሁ",
"body": "እንደ እነዚህ ነገሮች ጠንካራ መሆን እግዚአብሔር እንዲናገር የነገረውን ነገር ለመናገር ልበ ሙሉ መሆንና የማይለወጥ አቋም መያዝን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በምድሪቱ ሁሉ ላይ እንደ ተመሸገ ከተማ፣ እንደ ብረትም ዓምድ እና እንደ ናስ ቅጥር ጠንካራ አድርጌሃለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ብረት … ናስ",
"body": "እነዚህ በዚያን ጊዜ እጅግ በጣም ጠንካራ በመሆናቸው የሚታወቁ ነገሮች ነበሩ፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ምድሪቱ ሁሉ ",
"body": "ይህ የምድሪቱን ሕዝብ ሁሉ የሚወክል ነው፡፡ (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ከአንተ ጋር ይዋጋሉ",
"body": "ይህ የሚያመለክተው የይሁዳ ሕዝብን ነው፡፡"
},
{
"title": "ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው",
"body": "እግዚአብሔር እርሱ የተናገረው ቃል እንደሚፈጸም እርግጠኝነቱን ለመግለጽ ስለ ራሱ በስሙ ተናግሯል፡፡ በ ኤርምያስ 1:8 ላይ ይህን እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]