am_jer_tn/20/16.txt

38 lines
2.8 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ያ ሰው",
"body": "ይህ የሚያመለክተው ለኤርምያስ አባት የኤርምያስን መወለድ የነገረውን ሰው ነው"
},
{
"title": "ያህዌ የጣላቸው ከተሞች",
"body": "ይህ የሚያመለክተው ሰዶምን እና ገሞራን ነው፡፡"
},
{
"title": "እርሱ ርህራሄ የለውም",
"body": "እዚህ ስፍራ \"እርሱ\" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ያህዌን ነው፡፡"
},
{
"title": "እርሱ የለቅሶ ድምጽ ይስማ",
"body": "እዚህ ስፍራ \"እርሱ\" የሚለው ቃል የሚያመለክተው \"ያንን ሰው\" ነው፡፡"
},
{
"title": "እናቴን መቃብሬ አላደረግክም",
"body": "ኤርምያስ ገና እናቱ አርጋዛው ሳለች ቢሞት ይሻለው እንደነበረ የተናገረው የእናቱን ማህጸን እንደ መቃብሩ በማድረግ ነበር፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ለዘለዓለም ከማህጸን ባልወጣሁ",
"body": "ኤርምያስ ነብሰጡር እናቱ ለዘለዓለም ሳትወልደኝ እንዳረገዘችኝ በኖረች ብሎ ይናገራል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "መከራ እና ጭንቀት…ሀፍረት ለማየት ለምን ከማህጸን ወጣሁ?",
"body": "ኤርምያስ ይህንን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የተጠቀመው ለመወለድ ምንም መልካም ምክንያት እንዳልነበረ ለማማረር ነው፡፡ ይህ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ \"መከራ እና ጭንቀት… እንዲሁም ሀፍረት ለማየት ካልሆነ በስተቀር እኔ የምወለድበት ምንም መልካም ምክንያት አልነበረም፡፡\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "መከራ እና ጭንቀት ለማየት",
"body": "\"መከራ\" እና \"ጭንቅ\" የሚሉት ቃላት በመሰሩ ተመሳሳይ ትርጉም ሲኖራቸው የአበሳውን መጠን እና ጥልቀት ያጎላሉ፡፡ \"ብዙ መከራ ለመቀበል\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ቀኖቼ በሀፍረት ተሞሉ",
"body": "እዚህ ስፍራ \"ቀኖች\" የሚለው ቃል የሚወክለው የኤርምያስን የህይወት ዘመን ነው፡፡ \"ህይወቴ በሀፍረት ተሞላ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]