am_jer_tn/06/25.txt

26 lines
2.6 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "ኤርምያስ ለኢየሩሳሌም ሕዝብ ይናገራል፡፡ አንዳንድ ትርጉሞች እግዚአብሔር ለኢየሩሳሌም ሕዝብ እየተናገረ ነው ብለው ተርጉመውታል፡፡"
},
{
"title": "የጠላት ሰይፍና ድንጋጤ ከብቧችኋል",
"body": "“የጠላት ሰይፍ” የሚለው ሀረግ ከሰይፎቻቸው ጋር ለማጥቃት የተዘጋጁ ጠላቶችን ይወክላል፡፡ “ድንጋጤ” የሚለው ረቂቅ ስም ሰዎች እንዲፈሩ የሚያደርጉ ነገሮችን ያመለክታል፡፡ ይህ ደግሞ ከቅጽል ጋር ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠላቶች ከሰይፎቻቸው ጋር በሁሉም ስፍራ ስላሉ እያንዳንዱ ሰው በፍርሃት ይንቀጠቀጣል” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ and ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የሕዝቤ ሴት ልጅ",
"body": "እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንደ ሴት ጠርቶ በመናገር ለእነርሱ ያለውን ፍቅር ኤርምያስ ያሳያል፡፡ ይህን ተመሳሳይ ሀረግ በኤርምያስ 4:11 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ “እናንተ ለእኔ እንደ ሴት ልጅ የሆናችሁ ሕዝቤ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ማቅ ልበሺ በአመድም ላይ ተንከባለይ",
"body": "ሕዝብ እነዚህን ነገሮች የሚያደርገው ከመጠን በላይ የሆነ ሃዘን እንደተሰማቸው ለማሳየት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ማቅ በመልበስና በአመድ ላይ በመንከባለል ከመጠን በላይ እንዳዘንሽ አሳዪ” (ምሳሌያዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ለአንድያ ልጅ እንደሚደረግ ልቅሶ፣ መራራ ልቅሶ አልቅሺ",
"body": "ኤርምያስ የሕዝቡን ታላቅ ሃዘን እናት አንድያ ልጇ ሲሞትባት ከሚሰማት ሃዘን ጋር ያነጻጽረዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንድያ ልጅሽ እንደሞተባት እናት ሆነሽ መራራ ልቅሶ አልቅሺ” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አጥፊው በድንገት በላያችን ይመጣልና",
"body": "“ምክንያቱም የጠላት ጦር ሰራዊት እኛን ለማጥቃት በድንገት ይመጣልና”"
}
]