am_jer_tn/12/01.txt

18 lines
1.8 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "ኤርምያስ ለእግዚአብሔር እየተናገረ ነው፡፡"
},
{
"title": "ክፉዎች",
"body": "ይህ ክፉ ሰዎችን ይወክላ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉ ሰዎች” ወይም “ክፉ የሆኑ ሰዎች” (የስም ቅጽል የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አንተ ተክለሃቸዋል፣ ስርም ሰድደዋል፡፡ ፍሬ ማፍራትንም ቀጥለዋል",
"body": "እዚህ ላይ ኤርምያስ ስለ ክፉ ሰዎች ሲናገር የፍሬ ዛፎች እንደሆኑ አድርጎ ገልጦአቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተ እንደተከልሃቸው፣ እንዲለመልሙ እንዳደረግሃቸውና ብዙ ፍሬ እንዲያፈሩ እንዳደረግሃቸው ፍሬ እንደሚሰጥ ዛፍ ናቸው (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በአፋቸው አንተ ቅርብ ነህ፥ ከልባቸው ግን ሩቅ ነህ",
"body": "እዚህ ላይ “አፋቸው” የሚለው ሰው የሚናገረውን ነገር ይወክላል፡፡ “ልባቸው” የሚለው ደግሞ ሰው የሚያስበውንና ስሜቱን ይወክላል፡፡ በተጨማሪ ታማኝ መሆን ለሰው ቅርብ መሆን እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፣ ታማኝ አለመሆን ደግሞ ከሰው በጣም ሩቅ መሆን እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ ስለ አንተ ሁልጊዜ ጥሩ ነገር ይናራሉ ነገር ግን አንተን አይወዱህም ደግሞም አያከብሩህም” (ምትክ ስም እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]