am_jer_tn/02/23.txt

42 lines
4.8 KiB
Plaintext

[
{
"title": "በአሊምንም አልተከተልሁም እንዴት ትያለሽ? ",
"body": "እግዚአብሔር ይህን ጥያቄ የተጠቀመው ሕዝቡ በአሊምን አላመለክሁም ብሎ ለተናገረው ለመገሰጽ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “You lie when you say, ‘በአሊምንም አልተከተልሁም’ ብለሽ መናገርሽ ዋሽተሻል” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "መከተል",
"body": "ይህ ለማገልገልና ለማምለክ ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አንቺ እዚህና እዚያ የምትሮጥ ፈጣን ሴት ግመል ነሽ",
"body": "እግዚአብሔር እስራኤል ሌሎች አማልክትን ስለማምለካቸው ሲናገር ወንድ ግመል ለመፈለግና ከእርሱ ጋር ወሲብ ለማድረግ በሌላ አቅጣጫ እንደምትሮጥ ሴት ግመል አድርጎ ገልጿቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንቺ ወንድ ግመል ለመፈለግና ከእርሱ ጋር ወሲብ ለማድረግ ወደፊትና ወደኋላ እንደምትሮጥ ፈጣን ሴት ግመል ነሽ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ፈጣን",
"body": "በፍጥነት መሮጥ የምትችል"
},
{
"title": "በምኞትዋ ነፋስን እንደምታሸትት፥ በምድረ በዳ እንደ ለመደች እንደ ሜዳ አህያ ነሽ",
"body": "እግዚአብሔር እስራኤል ሌሎች አማልክትን ስለማምለካቸው ሲናገር ወንድ የሜዳ አህዮች ለመፈለግ እንደምትሮጥ ሴት የሜዳ አህያ አድርጎ ገልጿቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንቺ በምድረ በዳ እንደምትኖር ወጣት ሴት የሜዳ አህያ ነሽ፡፡ ወሲብ መፈጸም ስትፈልግ ከቁጥጥር ውጭ ትሆናለች፣ ወንድ የሜዳ አህያ ለመፈለግ ነፋስን ታሸትታለች” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በምኞትዋ",
"body": "ይህ ሀረግ ፈሊጥ ሲሆን የሚያመለክተው ሴት የሜዳ አህያ ከወንድ የሜዳ አህዮች ጋር ወሲብ ለመፈጸም የምትፈልግበትን ጊዜ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወሲብ ለመፈጸም ስትፈልግ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ከምኞትዋ የሚመልሳት ማን ነው? ",
"body": "ይህ ጥያቄ ጥቅም ላይ የዋለው ሴት የሜዳ አህያ ከወንድ የሜዳ አህያ ጋር ወሲብ ለመፈጸም ስትፈልግ ሊቆጣጠራት የሚችል ማንም እንደሌለ አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወሲብ መፈጸም ስትፈልግ ማንም ወደኋላ ሊመልሳት አይችልም፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እግርሽን ባዶ ከመሆን ጕሮሮሽንም ከውኃ ጥም ከልክዪ!",
"body": "እግዚአብሔር እስራኤል ሌሎች አማልክትን ለማምለክ ስለመፈለጋቸው ሲናገር እነዚህን አማልክት ለመፈለግ በምድረ በዳ ይሮጡ እንደነበር አድርጎ ገልጿቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነዚህን ሐሰተኛ አማልክት ለመፈለግ እዚህና እዚያ መሮጥሽን እንድታቆሚ ነግሬሻለሁ፣ ምክንያቱም ይህ ሁሉ ድርጊትሽ ውጤቱ ጫማሽ እንዲያልቅና በጣም እንድትጠሚ የሚያደርግ ነው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ተስፋ የለውም",
"body": "“ራሳችንን በመከልከል ምንም ዓይነት ተስፋ የለም፡፡” ይህ ሌሎች አማልክትን ከመከተል ራሳቸውን ማስቆም እንደማይችሉ የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ራሳችንን ፈጽሞ ማስቆም አንችልም” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አይሆንም፣ እንግዶችን ወድጄአለሁና፥ እከተላቸዋለሁም",
"body": "እዚህ ላይ “እንግዶች” የሚለው ባዕዳን አማልክትን የሚወክል ነው፣ እና “እከተላቸዋለሁ” የሚለው እነርሱን ማምለክ የሚወክል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ባዕዳን አማልክትን መከተልና እነርሱን ማምለክ አለብን!” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]