am_jer_tn/30/01.txt

22 lines
2.6 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ከያህዌ ዘንድ ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል፣ የመጣ ቃል",
"body": "ፈሊጡ የዋለው ከእግዚአብሔር ዘንድ ልዩ መልዕክት ለማስተዋወቅ ነው፡፡ ተመሳሳይ የሆነ ሀረግ በኤርምያስ 1፡4 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፤ እንደ አስፈላጊነቱም ግልጽ አድርጉት፡፡ \"ያህዌ ለኤርምያስ የሰጠው መልዕክት ይህ ነው፡፡ እንዲህ አለ\" ወይም \"ያህዌ ለኤርምያስ ይህንን መልዕክት ሰጠው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እነሆ ተመልከት",
"body": "\"በጥንቃቄ አድምጥ ፡፡\" ይህ ሀረግ ያህዌ ቀጥሎ የሚናገረውን በጥንቃቄ ለመስማት ትኩረት ይፈጥራል"
},
{
"title": "እኔ ሀብታችሁን የምመልስበት…ቀናቱ እየቀረቡ ነው",
"body": "የሀብት/ዕድል ጊዜ የተገለጸው \"ቀናት እየመጡ\" እንደሆነ ተደርጎ ነው፡፡ ይህ ዘይቤ በኤርምያስ 7፡32 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"ወደፊት … እድላችሁን አድሳለሁ\" ወይም \"እድላችሁን የማድስበት ጊዜ ይመጣል\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ የያህዌ አዋጅ/ትዕዛዝ ነው",
"body": "ያህዌ ስለ ራሱ በስሙ የሚናገረው/የሚምለው የተናገረው ነገር እርግጠኛ መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"ያህዌ ያዘዘው ይህንን ነው\" ወይም \"እኔ ያህዌ ያዘዝኩት ይህንን ነው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የህዝቤን የእስራኤልን እና ይሁዳን እድል ፈንታ አድሳለሁ",
"body": "\"ለህዝቤ ለእስራኤል እና ለይሁዳ ነገሮች ዳግም፣ መልካም እንዲሆኑ አደርጋለሁ\" ወይም \"ህዝቤ እስራኤል እና ይሁዳ ዳግም መልካም ህይወት እንዲኖሩ አደርጋለሁ፡፡\" በኤርምያስ 29፡14 ላይ ተመሳሳይ የሆኑ ቃላት እንዴት እንደ ተተረጎሙ ይመልከቱ፡፡"
}
]