am_jer_tn/14/01.txt

26 lines
2.2 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "እግዚአብሔር በነቢዩ በኤርምያስ በኩል ስለ ሕዝቡ አመንዝራነት ተናግሯል፡፡"
},
{
"title": "ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው",
"body": "ይህ ፈሊጥ ሲሆን ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣውን ልዩ መልእክት ለማስተዋወቅ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ ይህን ተመሳሳይ ሀረግ በኤርምያስ 1:4 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ይህ እግዚአብሔር ለኤርምያስ የሰጠው መልእክት ነው” ወይም “ይህ እግዚአብሔር ለኤርምያስ የተናገረው መልእክት ነው” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይሁዳ ታልቅስ",
"body": "እዚህ ላይ “ይሁዳ” በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የይሁዳ ሕዝብ ያልቅስ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ደጆችዋም ይፈራርሱ",
"body": "እዚህ ላይ “ደጆች” የሚለው ጠላቶችን ወደ ከተማ እንዳይገቡ የሚከለክልና ሰዎች የንግድና የመንግስት ስራ የሚሰሩበት ሲሆን ለይሁዳ ከተሞች ወካይ ነው፣ የይሁዳ ከተሞች ደግሞ በውስጣቸው ለሚኖሩ ሕዝቦች ምትክ ስም ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከተሞቿ ይፈራርሱ” ወይም “በከተሞቿ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ራሳቸውን ለመከላከል የሚችሉ አይሁኑ” (ወካይ ዘይቤ እና ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይፈራርሱ",
"body": "“ፍርስራሽ ወደመሆን ይለወጡ”"
},
{
"title": "ለኢየሩሳሌም የሚያደርጉት ጩኸት ከፍ ከፍ ብሎአል",
"body": "“ከፍ ብሏል” የሚለው ሀረግ ፈሊጥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለኢየሩሳሌም በጸሎት በታላቅ ጩኸት እየተጣሩ ነው” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]