am_jer_tn/13/25.txt

18 lines
2.2 KiB
Plaintext

[
{
"title": "እኔ ለአንቺ የሰጠሁሽ፣ ለአንቺ ያወጅኩልሽ ድርሻሽ ይህ ነው",
"body": "እነዚህ ሁለቱ ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆን በይሁዳ ሕዝብ ላይ እግዚአብሔር እንዲሆንባቸው የወሰነው እነዚህ ነገሮች እንደሆኑ አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በእናንተ ላይ እንዲሆን ያደረግሁት ነገር ይህ ነው” (ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው",
"body": "እግዚአብሔር የሚናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "እኔ ራሴ የልብስሽን ዘርፍ በፊትሽ እገልጣለሁ እፍረትሽም ይታያል",
"body": "ይህ እግዚአብሔር እፍረት እንዲሰማቸው ያደርጋቸዋል ማለት ነው፡፡ ይህን ሲል በየትኛውም መንገድ ይደፍራቸዋል ማለት አይደለም፡፡ ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ማንኛውም ሰው እፍረትሽን እንዲያይና እፍረት እንዲሰማሽ ለማድረግ እኔ ራሴ የልብስሽን ዘርፍ በፊትሽ እንደሚገልጥ እሆናለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ማሽካካት",
"body": "ይህ ወንድ ፈረስ ሴት ፈረስን ሲፈልግ የሚሰማው ድምጽ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “መመኘት” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]