am_jer_tn/13/22.txt

22 lines
2.9 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "እግዚአብሔር ለኤርምያስ መናገሩን ቀጥሏል፡፡ እርሱ ለይሁዳ ንጉስና ለንጉሱ እናት ምን እንደሚላቸው ለኤርምያስ እየነገረው ነው፡፡ "
},
{
"title": "የልብስሽ ዘርፍ ተገልጦአል ተረከዝሽም ተገፍፎአል",
"body": "ይህ የጠላት ጦር ሰራዊት አባላት የይሁዳን ሴቶች ይደፍሯቸዋል ማለት ነው፡፡ ይህ በገቢር ቅርጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የጠላት ጦር ሰራዊት አባላት የሴቶቻችሁን ቀሚስ እየገለቡ ይደፍሯቸዋል፡፡ (ለስላሴ እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በውኑ የኩሽ ሕዝብ የቆዳውን ቀለም ወይስ ነብር ዝንጕርጕርነትን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን?",
"body": "ይህ መልስ የማይሰጥበት ጥያቄ ጥቅም ላይ የዋለው የአንድ የማይቻልን ነገር ምሳሌ ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ ጥያቄ እንደ ዓረፍተ ሃሳብ ሊጻፍ ይችላል፡፡ በተጨማሪ “ይችላል” የሚለው ግልጽ ግስ በሁለተኛው ሀረግ ሊቀርብ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የኩሽ ሕዝብ የቆዳውን ቀለም ሊለውጥ አይችልም፣ ነብር ደግሞ ዝንጕርጕርነትን ይለውጥ ዘንድ አይችልም፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች እና አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እንዲህ ከሆነ ምንም እንኳ ክፋትን የለመዳችሁ ብትሆኑም እናንተ ደግሞ በጎ ለማድረግ ትችላላችሁ",
"body": "ይህ ዓረፍተ ሃሳብ ምጸታዊ ነው ምክንያቱም ስለ ኩሽ ሕዝብና ስለ ነብር የተሰጠው ምሳሌ የማይቻሉ ሁኔታዎች ናቸው፡፡ እነዚህ የማይቻሉ ነገሮች የተቻሉ ከሆነ እነርሱም መልካም ማድረግ እንደሚችሉ ያብራራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነዚህ ነገሮች የማይቻሉ እንደሆኑ እንደዚሁ ሁልጊዜ ክፋትን ማድረግ ለለመዳችሁ ለእናንተ መልካምን ማድረግ አይቻላችሁም” (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የምድረ በዳ ነፋስ ብትንትኑን እንደሚያወጣው ገለባ እንዲሁ እበታትናችኋለሁ",
"body": "“በነፋስ እንደሚበታተን ገለባ እንዲሁ እበታትናችኋለሁ፡፡” ገለባ በነፋስ እንደሚበታተን እንደዚሁ እግዚአብሔር ሕዝቡን በዓለም ዙርያ እንደሚበታትናቸው እየተናገረ ነው፡፡ (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]