am_jer_tn/03/23.txt

38 lines
4.1 KiB
Plaintext

[
{
"title": "በእርግጥ መታለል ከኮረብቶች ይመጣል",
"body": "እዚህ ላይ “ኮረብቶች” የሚለው ሕዝቡ በኮረብቶች ላይ የሚያደርጉትን የሐሰተኛ አማልክት አምልኮ ይወክላል፡፡ አሁን ሕዝቡ እነዚህ ሐሰተኛ አማልክት እነርሱን ሊመሩአቸውና ሊረዱአቸው እንደማይችሉ አውቀዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኛ በኮረብቶች ላይ የምናመልካቸው ሐሰተኛ አማልክት ሊመሩን አይችሉም” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ከተራሮች የሚመጣ ግራ የሚያጋባ ጩኸት ",
"body": "ሰዎች ሐሰተኛ አማልክትን በኮረብቶችና በተራሮች ላይ ሲያመልኩ ብዙ ጩኸት ያሰማሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኛ ሐሰተኛ አማልክትን ስናመልክ በተራሮች ላይ ግራ የሚያጋባ ጩኸት እናሰማለን ነገር ግን እነርሱ እኛን አይረዱንም” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመለክቱ)"
},
{
"title": "በእውነት የእስራኤል መዳን በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ ነው",
"body": "“በእውነት የእስራኤል አዳኝ አምላካችን እግዚአብሔር ነው” ወይም “በእውነት እስራኤልን ሊያድን የሚችል ብቸኛው አምላካችን እግዚአብሔር ነው”"
},
{
"title": "ነውረኛ ጣዖቶች አባቶቻችን የሰሩትን ሁሉ በሉት",
"body": "ይህ የእስራኤል ሕዝብ ያላቸውን ንብረት ሁሉ ለጣዖቶች መስዋዕት አድርገው ከማቅረባቸው የተነሳ ብዙ ሀብታቸውን ማጣታቸውን የሚወክል ነው፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በጎቻቸውንና ከብቶቻቸውን፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን",
"body": "ይህ የእስራኤል ሕዝብ ለጣዖቶች እያረዱ መስዋዕት አድርገው ያቀረቡት የእንስሳትና የሰዎች ዝርዝር ነው፡፡"
},
{
"title": "እንግዲህ እፍረታችንን ተከናበን እንተኛ፤ ውርደታችንም ይሸፍነን",
"body": "እነዚህ ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም ይጋራሉ፣ ደግሞም ሕዝቡ ነውረኛ ባህርያቸውን ሙሉ በሙሉ እንደተገነዘቡ አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሙሉ በሙሉ ራሳችንን እናዋርድ” (ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ውርደታችንም ይሸፍነን",
"body": "ውርደታቸውን ሙሉ በሙሉ መገንዘባቸው ውርደት እንደ ብርድ ልብስ ወይም ጨርቅ እነርሱን እንደሸፈናቸው ተደርጎ ተነግሯል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ከልጅነታችን ጊዜ ጀምሮ ",
"body": "ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) “ከልጅነታችን ጊዜ ጀምሮ” የሚለው እያንዳንዱ ሰው ወጣት የነበረበትን ጊዜ ያመለክታል፡፡ ወይም 2) “ከልጅነታችን ጊዜ ጀምሮ” እስራኤል መጀመርያ ሕዝብ የሆነችበትን ጊዜ የሚያመለክት ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “መጀመርያ ሕዝብ ከሆንንበት ጊዜ ጀምሮ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የአምላካችንንም የእግዚአብሔርን ድምፅ አልሰማንም",
"body": "እዚህ ላይ “መስማት” መታዘዝን ይወክላል፣ “የእግዚአብሔር ድምፅ” ደግሞ እግዚአብሔር የተናገረውን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አምላካችን እግዚአብሔር የተናገረውን አልታዘዝንም” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]