am_jer_tn/23/35.txt

22 lines
2.7 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አያያዥ ሃሳብ፡",
"body": "ያህዌ ስለ ሀሰተኛ ነቢያት እና ካህናት በ23፡9 ላይ የጀመረውን እና በኤርምያስ 23፡40 ላይ የሚጨርሰውን መልዕክቱን ማድረሱን ይቀጥላል፡፡"
},
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡",
"body": "ከቁጥር 33-40 ድረስ \"ሸክም\" የሚለውን ቃል በመደጋገም የሚደረግ አገላለጽ አለ፡፡ አንዳንዴ \"መልዕክተኛ\" ማለት ሲሆን በሌላ ጊዜ \"ለመሸከም ከባድ የሆነ ሸክም\" ማለት ይሆናል፡፡ ከተቻለ ይህ የቃላት ድግግም አገላለጽ እንዳለ ሊጠበቅ ይገባዋል፡፡ "
},
{
"title": "እናነተ እንዲህ ማለታችሁን ትቀጥላላችሁ… ‘ያህዌ የተናገረው ምንድን ነው?'",
"body": "ይህን ዐረፍተ ነገር መመዝገብ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ \"እያንዳንዱ ሰው ወዳጁን እና ወንድሙን ‘ያህዌ ምን ምላሽ ሰጠ?' ደግሞም ‘ያህዌ ምን ትዕዛዝ ሰጠ/ምን አለ?'\" ብሎ መጠየቁን ይቀጥላል፡፡ "
},
{
"title": "ነገር ግን ከእንግዲህ በኋላ ‘ስለ ያህዌ ሸክም መናገር አይኖርባችሁም፣ ምክንያቱም ሸክሙ የእያንዳንዱ ሰው ቃል የራሱ ሸክም ነው፣ እናም",
"body": "ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ሁለቱም \"የሸክም\" ሁኔታዎች ትርጉማቸው \"መልዕክት\" ማለት ነው፡፡ \"ከእንግዲህ ህልማችሁን ‘የያህዌ ሸክም' ብላችሁ መጥራት የለባችሁም ምክንያቱም እነዚያ የእያንዳንዱ ሰው የራሱ ቃሎች ብቻ ናቸው፣ እናም\" ወይም 2) የመጀመሪያው ‘ሸክም' የሚለው ትርጉም \"መልዕክት\" ማለት ሲሆን የሁለተኛው ትርጉም \"ከባድ ሸክም\" ማለት ነው፡፡ \"ከእንግዲህ ‘ስለ ያህዌ መልዕክት' መናገር የለባችሁም ምክንያቱም እያንዳንዳችሁ የምትናገሯቸው ቃላት በዚህ መንገድ ‘ከባድ ሸክም' የሆኑ ናቸው፡፡\" "
},
{
"title": "እናንተ የአምላካችንን ቃሎች… ገልብጣችኋል",
"body": "አንድን ነበር \"መገልበጥ\" ያንን ነገር ማጣመም ወይም መልኩን ማበላሸት ነው፡፡ \"እግዚአብሔር የተናገረውን ሳይሆን እናንተ ማለት የፈረጋችሁትን ለመናገር የሰራዊት ጌታ የህያው እግዚአብሔርን መልዕክት ቀይራችኋል\""
}
]