am_jer_tn/05/30.txt

30 lines
2.5 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "እግዚአብሔር መናገሩን ቀጥሏል፡፡"
},
{
"title": "ግፍና አሰቃቂ ነገር ተከስቷል",
"body": "ይህ በገቢር ቅርጽ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች በጣም አስደንጋጭና አሰቃቂ ነገሮች ይፈጽማሉ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በምድሪቱ",
"body": "እዚህ ላይ “ምድሪቱ” የሚለው የአስራኤልን ምድር ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በእስራኤል ምድር” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ነቢያት በማጭበርበር ትንቢት ይናገራሉ፣ ካህናትም በራሳቸው ኃይል ያስተዳድራሉ",
"body": "እነዚህ በቁጥር 30 ላይ የተነገሩት ግፎችና አሰቃቂ ነገሮች ናቸው፡፡"
},
{
"title": "ነቢያት በማጭበርበር ትንቢት ይናገራሉ ",
"body": "“ነቢያቱ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ” ወይም “ነቢያቱ ትንቢት ሲናገሩ ውሸትን ይናራሉ”"
},
{
"title": "ካህናትም በራሳቸው ኃይል ያስተዳድራሉ",
"body": "ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ካህናቱ ለእግዚአብሔር ስልጣን ራሳቸውን አላስገዙም፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ካህናቱ በራሳቸው ስልጣን ያስተዳድራሉ” ወይም 2) ካህናቱ ነቢያቱ በሚሰጡአቸው መመርያ መሰረት ያስተዳድራሉ (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ነገር ግን በመጨረሻ ምን ይሆናል?",
"body": "“ነገር ግን ይህ ከሆነ በኋላ በመጨረሻ ምን ታደርጋላችሁ?” እግዚአብሔር ይህን ጥያቄ የተጠቀመው እርሱ ለሰሩት ስራ ሲቀጣቸው ክፉ ስለመሆናቸው እንደሚጸጸቱ አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ነገር ግን በመጨረሻ እኔ እቀጣችኋለሁ፣ እናንተም ስለ ክፉ ድርጊታችሁ ትጸጸታላችሁ” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች እና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]