am_jer_tn/12/16.txt

34 lines
3.5 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "ስለ ይሁዳ ጎረቤቶች የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል"
},
{
"title": "እንዲህ ይሆናል",
"body": "“እንዲህ ይፈጸማል”"
},
{
"title": "ሕያው እግዚአብሔርን",
"body": "“እግዚአብሔር በእርግጠኝነት ሕያው እንደሆነ ሁሉ፡፡” ሕዝቡ ይህን መግለጫ የሚጠቀሙት ቀጥለው የሚናገሩት ነገር በእርግጠኝነት እውነት እንደሆነ ለማሳየት ነው፡፡ ይህ የማይናወጥ ቃል ኪዳን የማድረግ መንገድ ነው፡፡ ከበኣል ስም ይልቅ በእግዚአብሔር ስም መማል እነርሱ ከበኣል ይልቅ እግዚአብሔርን እንደሚያመልኩ ያመለክታል፡፡ ይህን ኤርምያስ 4:2 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ በማይናወጥ መልኩ እምላለሁ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በሕዝቤ መካከል ይመሠረታሉ",
"body": "ይህ የሚናገረው ስለ ሕዝቡ ባለጠጋ መሆን ሲሆን የተገነባ ሕንጻ እንደሆኑ ተደርገው ተገልጸዋል፡፡ ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ እነርሱን በሕዝቤ መካከል እመሰርታቸዋለሁ” ወይም “እኔ እነርሱን ባለጠጋ አደርጋቸዋለሁ፣ እነርሱም በሕዝቤ መካከል ይኖራሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "መካከል",
"body": "መኃል"
},
{
"title": "ያንን ሕዝብ ፈጽሜ እነቅለዋለሁ፡፡ በእርግጠኝነት ይነቀላል፣ ይጠፋልም",
"body": "እግዚአብሔር ሕዝቡ ምድራቸውን እንዲለቅቁ ስለማስገደዱና መንግስታቸውን ስለማጥፋቱ ሲናገር ከመሬት ነቅሎ እንደሚያወጣቸው ተክሎች እንደሆኑ አድርጎ ገልጾአቸዋል፡፡ እነዚህ ሁለት ዓረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው ስለዚህ አንድ ላይ ሊጣመሩ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ ይህን ሕዝብ በእርግጠኝነት በግዞት እንዲኖር አደርጋለሁ መንግስቱንም አጠፋለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በእርግጠኝነት ይነቀላል፣ ይጠፋልም",
"body": "ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ በእርግጠኝነት እነቅለዋለሁ፣ አጠፋውማለሁ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው",
"body": "እግዚአብሔር የሚናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ) "
}
]