am_jer_tn/08/18.txt

38 lines
3.5 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "ኤርምያስና እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ሕዝብ ንግግር ያደርጋሉ፡፡"
},
{
"title": "የእኔ ሃዘን አያልቅም",
"body": "እዚህ ላይ “የእኔ” የሚለው ኤርምያስን ያመለክታል፡፡ የመጀመርያው የተጻፈበት ሃሳብ ግልጽ አይደለም ስለዚህ በዘመኑ ባሉት ትርጉሞች በተለያዩ መንገዶች ተተርጉሟል፡፡"
},
{
"title": "አያልቅም",
"body": "ይህ ቃል የኤርምያስን ጥልቅ ሃዘን ለመግለጽ ጥቅም ላይ የዋለ ግነት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በጣም ታላቅ” ነው፡፡ (ግነት/ግነታዊ ቋንቋ እና ጅምላ ፍረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ልቤ ትምሟል",
"body": "እዚህ ላይ “ልብ” የሚለው ኤርምያስን የሚወክል ሲሆን እርሱ የተሰማውን ነገርና ስሜቱን አጽንዖት የሚሰጥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ በጥልቅ የውስጥ ማንነቴ ሕመም ይሰማኛል” (ወካይ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እነሆ!",
"body": "ይህ ከዚህ ቀጥሎ ለሚነገረው ነገር አንባቢው ትኩረት እንዲሰጥ የሚያነቃ ነው፡፡ “ትኩረት ስጥ”"
},
{
"title": "የሕዝቤ ሴት ልጅ",
"body": "ኤርምያስ ለሴት ልጅ የሚገባውን ዓይነት ፍቅሩን ለይሁዳ ሕዝብ በሚያሳይበት መንገድ ስለ እነርሱ ይናገራል፡፡ ይህንን በኤርምያስ 4፡11 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእኔ ውድ ሕዝቤ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ከሩቅ አገር",
"body": "ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ከግዞት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከግዞት ከሩቅ አገር” ወይም 2) ከይሁዳ ምድር በሙሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በምድራችን ዙርያ ሁሉ”"
},
{
"title": "እግዚአብሔር በጽዮን የለምን? ወይስ ንጉስዋ በእርስዋ ዘንድ የለምን?",
"body": "እነዚህ ሁለት ጥያቄዎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ የይሁዳ ሕዝብ እግዚአብ|ሔር ለምን እነርሱን እንዳላዳናቸው ግራ እንደተጋቡ የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር በጽዮን ንጉስ ከሆነ ለምን እርሱ እኛን አላዳነንም?” (ትይዩነት/ተመሳሳይነት እና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ እና መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በተቀረጹ ምስሎቻቸውና እንዲሁም ከንቱ በሆኑ ባዕዳን ጣዖታት እኔን ለምን አስቆጡኝ?",
"body": "“እኔን” የሚለው ቃል እግዚአብሔርን ያመለክታል፡፡ ይህ ጥያቄ በዓረፍተ ሃሳብ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ እኔ እንዳድናቸው የሚፈልጉ ከሆነ በተቀረጹ ምስሎቻቸው እኔን ሊያስቆጡኝ አይገባም” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ )"
}
]