am_jer_tn/10/23.txt

26 lines
2.8 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "ኤርምያስ ለእስራኤል ሕዝብ ይጸልያል፡፡"
},
{
"title": "የሰው መንገድ ከራ አይደለም፡፡ የሚራመድ ሰው አንዱም ቢሆን የራሱን መንገድ አያቀናም",
"body": "እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ይህን ሲል አንድ ሰው በሕይወት ጉዞው በእርሱ ላይ በሚሆኑት በተለያዩ ነገሮች ላይ በበላይነት ራሱ ሊቆጣጠረው አይችልም ለመለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ማንም ሰው በእርሱ ላይ የሚሆነውን ነገር መቆጣጠር አይችልም፣ ማንም ሰው በሕይወቱ የሚከናወነውን ነገር ራሱ አቅጣጫ ማስያዝ አይችልም” (ትይዩነት/ተመሳሳይነት እና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ቁጣህን በመንግስታት ላይ አፍስሰው",
"body": "እዚህ ላይ “መንግስታት” የሚለው በውስጣቸው የሚኖሩትን ሕዝብ የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በቁጣህ መንግስታትን ቅጣቸው” ወይም “በቁጣህ የሕዝቦችን መንግስታት ቅጣቸው” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱጉም፡- "
},
{
"title": "ስምህን በማይጠሩ",
"body": "ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተን የማያመልኩ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ያዕቆብን አሟጥጠው ስለበሉት፣ ፈጽመው ስለዋጡት፣ ሙሉ በሙሉ እርሱን ስላጠፉት ",
"body": "እነዚህ ሶስት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ እስራኤልን ሙሉ በሙሉ መጥፋት አጽንዖት ጠት ኤርምያስ ይህንን ሃሳብ ሶስት ጊዜ ደጋግሞታል፡፡ ይህ የሚናገረው የእስራኤልን ሕዝብ ስላጠቁት የጠላት ጦር ሰራዊት ሲሆን ጦር ሰራዊቱ የሚበላውን እንስሳ ፈልጎ እንደሚያጠቃና እንደሚበላ ሃይለኛ ተናካሽ እንስሳ ተደርጎ ተገልጦአል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ የእስራኤልን ሕዝብ በሃይል አጥቅተውታልና ደግሞም እነርሱን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋ በልተዋቸዋልና” (ትይዩነት/ተመሳሳይነት እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "መኖርያቸውን ወና አድርገውታል",
"body": "“ቤታቸውን ወና አድርገውታል”"
}
]