am_jer_tn/24/08.txt

26 lines
2.3 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ነገር ግን ለመበላት እጅግ መጥፎ እንደሆኑት መጥፎ በለሶች",
"body": "ይህ ተነጻጻሪ ዘይቤ በእየሩሳሌም ስላሉ ክፉ ባለስልጣናት ለመበላት እጅግ እንደ ተበላሹ እንደ መጥፎ በለሶች አድርጎ ይገልጻል፡፡ መጥፎ በለሶች አንዳች ጥቅም እንደሌላቸው ሁሉ፣ እነዚህ ያህዌን የማይከተሉ ሰዎችም ጥቅም የሌላቸው ናቸው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ወደ አስፈሪ ነገር ወደ ጥፋት እለውጣቸዋለሁ… የተዋረዱ እና መነጋገሪያ፣ መነረጓጠጫ እና ለእርግማን አደርጋቸዋለሁ",
"body": "እነዚህ ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም ሲኖራቸው፣ ያህዌ የእየሩሳሌምን ሰዎች እንዴት በጥብቅ እንደሚፈርድባቸው ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ ሌሎች ሰዎች የደረሰባቸውን ሲመለከቱ ይፈራሉ፡፡ (ጥንድ ትርጉም እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በእነርሱ ላይ ሰይፍ፣ ችጋር፣ እና መቅሰፍት እልክባቸዋለሁ",
"body": "\"በጦርነት፣ በችጋር እና በበሽታ አገድላቸዋለሁ\""
},
{
"title": "ሰይፍ እሰዳለሁ",
"body": "እዚህ ስፍራ \"ሰይፍ\" ጦርነትን እና የጠላትን ሰራዊቶች ያመለክታል፡፡ \"እኔ የጠላትን ሰራዊት እልካለሁ\" ወይም \"ጦርነት እሰዳለሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሰይፍ፣ ችጋር፣ እና መቅሰፍት",
"body": "እነዚህ ነገሮች የተነገሩት የእየሩሳሌምን ሰዎች ሊያጠቁ እንደሚችሉ ህይወት እንዳላቸው ነገሮች ተደርገው ነው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እነርሱ ከምድሪቱ ተደምስሰዋል",
"body": "\"አንዳቸውም በምድሪቱ አልቀሩም\" "
}
]