am_jer_tn/44/29.txt

30 lines
2.2 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ይላል እግዚአብሄር",
"body": "እግዚአብሄር ራሱን በስሙ የገለጸበት ምክንያት ቃሉን አስረግጦ ለመናገር ስለፈለገ ነው፡፡፤ ኤርምያስ 1፡8 የተተረጎመበትን መንገድ ይመልከቱ፡፡ ‹‹እግዚአብሄር የተናገረው ይህንን ነው›› ወይም ‹‹እኔ እግዚአብሄር የተናገርኩት ይህንን ነው››"
},
{
"title": "…እንድቀጣችሁ",
"body": "እግዚአብሄር እንደተቃወማቸውና እንደሚቀጣቸው እየተናገረ ነው"
},
{
"title": "ቃሌም በላያችሁ ለክፋት እንዲጸና ታውቁ ዘንድ ",
"body": "እግዚአብሄር በቃሉ ክፋትን እንደሚያፀና ሲናገር እንደ ቃሉ እንደ ሚያጠቃቸው መስሎ ይናገራል፡፡ “እኔ የተናገርኩት ይሆናል ክፉም ነገር ይሆንባችኋል”"
},
{
"title": "እነሆ",
"body": "ተመልከት ወይም ልብ በል"
},
{
"title": "የግብጹን ንጉሥ ፈርዖን ሖፍራን ለጠላቶቹ ነፍሱንም ለሚፈልጉ እጅ አሳልፌ እሰጠዋለሁ",
"body": "“እጅ” የሚለው ሀይል ወይም ጉልበትን ያመለክታል፡፡ “የግብጹን ንጉሥ ፈርዖን ሖፍራን እንዲያሸንፉት እሱን ለመግደል የሚፈልጉት ለጠላቶቹ እፈቅዳለሁ”"
},
{
"title": "ሖፍራን",
"body": "ይህ የሰው ስም ነው፡፡"
},
{
"title": "የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን ጠላቱ ለሆነው ነፍሱንም ለፈለገው ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እንደ ሰጠሁት",
"body": "“እጅ” የሚለው ሀይል ወይም ጉልበትን ያመለክታል፡፡ ናቡከደነፆር የሚያመለክተው አጠቃላይ ሰራዊቱን ነው፡፡ “ነፍሱን ለፈለገው” የሚለው ቃል መግደልን ያመለክታል፡፡ “የናቡከደነፆር ሰራዊት የይሁዳን ንጉስ ሴዴቅያስን እንዲያሸንፉ ሳደርግ”"
}
]