am_jer_tn/49/23.txt

42 lines
2.6 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ ሀሳብ",
"body": "እግዚአብሄር ለደማስቆ ህዝቦች የሚሆነውን ተናገረ"
},
{
"title": "ሐማትና አርፋድ አፈሩ ቀለጡም",
"body": "“ሐማት” እና ”አርፋድ” በውስጣቸው የሚኖሩትን ህዝቦች ያመለክታል፡፡ “በሐማት እና አርፋድ የሚኖሩ ህዝቦች አፈሩ ቀለጡም”"
},
{
"title": "ሐማትና አርፋድ",
"body": "በሶሪያ የሚገኙ ከተማዎች ናቸው"
},
{
"title": "ይቀልጣሉ",
"body": "የአንድ ሰው ፍራቻን እንደ መቅለጥ መስሎ ይናገራል፡፡ “እጅግ በጣም ይፈራሉ”"
},
{
"title": "በባህርም ላይ ሀዘን አለ ታርፍም ዘንድ አትችልም",
"body": "የባህር ውሃ ሁልጊዜ ይንቀሳቀሳል አያርፍምም፡፡ ይህን ከሚሰማው መጥፎ ዜና እና ጭንቀት የተነሳ የማያርፉትን ህዝቦች ጋር ያነፃፅራል፡፡"
},
{
"title": "ደማስቆ ደከመች ትሸሽም ዘንድ ዘወር አለች",
"body": "ደማስቆ የሚለው በውስጡ የሚኖሩትን ህዝቦች ያመለክታል፡፡ “የደማስቆ ህዝቦች ደከሙ ይሸሹም ዘንድ ዘወር አሉ”"
},
{
"title": "እንቅጥቅጥም ያዛት",
"body": "እንቅጥቅጥም የሚለው ፍራቻን ያመለክታል፡፡ “የደማስቆ ህዝብም ፍራቻ አደረባቸው”"
},
{
"title": "እንደ ወላድም ሴት ጣርና ምጥ ያዛት።",
"body": "ህዝቡ እንደ ምጥ ውስጥ እንዳለች ሴት አርጎ ይናገራል ይህም ያለውን ጭንቀት እና ፍርሃት አጉልቶ ያሳያል፡፡ “እንደ ወላድ ሴት ምጥ እንደያዛት ህዝቡ በትልቅ ጭንቀት እና ፍርሃት ላይ ናቸው”"
},
{
"title": "የተመሰገነችው ከተማ የደስታዬ ከተማ ሳትለቀቅ እንዴት ቀረች",
"body": "እግዚአብሄር እንዲህ አይነት ጥያቄዎችን ህዝቡ ከተማዋን እንዲለቁ የሚናገር ነው፡፡ “ይህ የተመሰገነች ከተማ የደስታዬ ከተማ አሁን ከተማዋን ህዝቡ ይልቀቅ”"
},
{
"title": "የተመሰገነችው ከተማ የደስታዬ ከተማ ሳትለቀቅ እንዴት ቀረች",
"body": "አንዳንዶች የደማስቆ ህዝቦች እንደተናገሩት ይገመታል፡፡ “የደማስቆ ህዝቦች እንዲህ አሉ “የተመሰገነችው ከተማ የደስታዬ ከተማ አሁን ባዶ ቀረች””"
}
]