am_jer_tn/46/15.txt

26 lines
2.3 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ኃይለኞችህ ስለ ምን ተወገዱ? እግዚአብሔር ስላደከማቸው አልቆሙም",
"body": "አንዳንድ የመፅሀፍ ቅዱስ ትርጉም “ሃያሉ አምላካችሁ አጲስ ስለምን ወደቀ እግዚአብሄ ስለመታው አደልምን” ብሎ ይተረጉመዋል፡፡ አጲስ የሚለው የበሬ ቅርፅ ያለው የግብፃውያን ጣኦት ነው፡፡ ይህ በሬ አብዛኛውን ጊዜ ሃይልን ያመለክታል፡፡ ለዚህም ነው አንዳንድ የመፅሀፍ ቅዱስ ትርጉሞች ሃይሎች ወይም ብርቱዎች የሚሉትን ቃሎች ሰራዊቱን እንደሚያመለክት ያሳያል፡፡"
},
{
"title": "ኃይለኞችህ ስለ ምን ተወገዱ? እግዚአብሔር ስላደከማቸው አልቆሙም",
"body": "እግዚአብሄር ይህን ጥያቄ የግብፃውያንን ሰራዊት ሃይል ላይ ለመቀለድ ሲጠቀም ያሳያል፡፡ “ሰራዊቶችህ ተወግደዋል ደግሞም እንደወደቁ ይቀራሉ አይነሱም”"
},
{
"title": "ብዛታቸውም ተሰናከለ፥ ሰውም አንዱ በአንዱ ላይ ወደቀ",
"body": "እግዚአብሄር ብዙ ሰራዊቶችን እርስ በእርስ እንዲወድቁ አደረገ"
},
{
"title": "ከሚያስጨንቅ ሰይፍ ፊት ወደ ወገናችን ወደ ተወለድንባት ምድር እንመለስ ",
"body": "“ሰይፍ” የሚለው የጦር እቃ የያዙ ሰራዊቶችን ያመለክታል፡፡ “ከሚያስጨንቀን ከጠላቶቻችን ፊት ወደ ወገናችን ወደ ተወለድንባት ምድር እንመለስ”"
},
{
"title": "…ጠሩት",
"body": "ጠሩት ሲል የሚያመለክተው (1) በግብፅ ያሉትን ሰዎች ሁሉ (2) ወደሀገራቸው ይሸሹ የነበሩትን የኩሽ፣ ፑት እና የሉድ ሰራዊትን"
},
{
"title": "የግብሥ ንጉሥ ፈርዖንን፦ ሰዓቱን የሚያሳልፍ ጕረኛ ብለው ጠሩት",
"body": "“ጉረኛ” የሚለው አንድ ሰው አደርጋለሁ ብሎ የሚናገር ነገር ግን የተናገረውን የማያደርግ ሲሆን ነው፡፡ “ፈንኦን አደርጋለሁ እያለ ያወራል ነገር ግን አያደርግም”"
}
]