am_jer_tn/46/11.txt

26 lines
1.6 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ ሃሳብ",
"body": "እግዚአብሄር ለግብፅ የሚናገረውን ጨረሰ"
},
{
"title": "ወደ ገለዓድ ውጪ የሚቀባንም መድኃኒት ውሰጂ",
"body": "ገለዓድ የሚባለው ስፍራ ታዋቂ የሆነ መድሃኒት የሚቀምሙ ሰዎች ያሉበት ስፍራ ሲሆን እግዚአብሄር መድሃኒት እንደማረዳቸው እያወቀ መድሃኒት ውሰዱ እያለ ይቀልድባቸዋል፡፡"
},
{
"title": "ድንግሊቱ የግብፅ ልጅ ሆይ",
"body": "የግብፅ ሀገር ህዝቦች እንደ ድንግል ልጅ መስሎ ይናገራል፡፡ “የግብፅ ህዝቦች”"
},
{
"title": "ጉስቁልና",
"body": "ይህ ክብር ማጣት ወይም የማፈር ስሜት ነው፡፡"
},
{
"title": "ለቅሶሽም ምድርን ሞልቶአታል",
"body": "“ምድርን” ሲል በምድር ላይ ያሉ ሰዎችን እና በግብፅ ላይ የደረሰውን የሚያውቁ ህዝቦችን ነው፡፡ የግብፃውያንን ለቅሶ የሚሰሙ ህዝቦች ሁሉ እንደ ለቅሶአቸው ምድርን እንደሞላ መስሎ ይናገራል፡፡ “በምድር ላይ ያሉ ህዝቦች ሁሉ ለቅሶሽን ይሰሙታል” "
},
{
"title": "ኃያሉ በኃያሉ ላይ ተሰናክሎ ሁለቱ በአንድነት ወድቀዋልና",
"body": "ሃያላን በጦርነት መሞታቸውን እንደ ተሰናክለው እንደወደቁ መስሎ ይናገራል፡፡ “የጦር ሰራዊታችሁ በጦርነት ይሞታሉ”"
}
]