am_jer_tn/45/04.txt

34 lines
2.5 KiB
Plaintext

[
{
"title": "እንዲህ በለው",
"body": "እግዚአብሄር ኤርምያስን ለባሮክ እንዲናገረው አዘዘው፡፡"
},
{
"title": "የሠራሁትን አፈርሳለሁ፥ የተከልሁትንም እነቅላለሁ",
"body": "ሁለቱም የሚናገሩት አንድ አይነት ሀሳብ አላቸው፡፡ እግዚአብሄር የይሁዳን ከተማና ህዝብ እንደሚያጠፋ ልክ እነደ ሚፈራርስ ግንብ እና ሊነቀል እንደሚችል ተክል መስሎ ይናገራል፡፡ “ይህ ከተማ ልክ እኔ እንደገነባሁት አፈራርሰዋለሁ፤ ልክ እንደተከልኩት ተክል አሁን ከተተከለበት እነቃቅለዋለሁ፡፡”"
},
{
"title": "ለራስህ ታላቅን ነገር ትፈልጋለህን?",
"body": "እግዚአብሄር ይህን ጥያቄ ባሮክ ሌሎች በጥሩ ሁኔታ እንዲንከባከቡት መፈለጉን ለማመልከት ይጠቀመዋል፡፡ “ለራስህ ጥሩን ነገር እንደምትፈልግ አውቃለሁ” ወይም “ሌሎች እንዲያከብሩህ እንደምትፈልግ አውቃለሁ”"
},
{
"title": "እነሆ",
"body": "ተመልከት ወይም ልብ በል"
},
{
"title": "በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ፥ እነሆ፥ ክፉ ነገርን አመጣለሁና",
"body": "ክፉ ነገርን አመጣለሁ ሲል እንደ ሚጓዝ እና የሆነ ቦታ እንደሚደርስ ነገር መስሎ ይናገራል፡፡ “ስጋ የለበሰን ሁሉ ክፉ ነገርን እንዲገጥመው አደርጋለሁ”"
},
{
"title": "ይላል እግዚአብሄር",
"body": "እግዚአብሄር ራሱን በስሙ የገለጸበት ምክንያት ቃሉን አስረግጦ ለመናገር ስለፈለገ ነው፡፡፤ ኤርምያስ 1፡8 የተተረጎመበትን መንገድ ይመልከቱ፡፡ ‹‹እግዚአብሄር የተናገረው ይህንን ነው›› ወይም ‹‹እኔ እግዚአብሄር የተናገርኩት ይህንን ነው››"
},
{
"title": "ነፍስህን እንደ ምርኮ አድርጌ እሰጥሃለሁ።",
"body": "ባሮክን እንዲያመልጥና በህይወት መኖሩን እንደ ተማረከ መስሎ ይናገራል፡፡ “ነገር ግን በሄድክበት ቦታ ሁሉ እጠብቅሀለሁ እናም በህይወት ትኖራለህ”"
},
{
"title": "ምርኮ",
"body": "በሃይል እና በጉልበት መውሰድ "
}
]