am_jer_tn/33/14.txt

50 lines
5.3 KiB
Plaintext

[
{
"title": "እነሆ/እዩ",
"body": "\"በጥንቃቄ አድምጡ\""
},
{
"title": "እኔ የምሰራባቸው…ቀናት እየመጡ ነው",
"body": "መጪው ጊዜ የተነገረው \"ቀናት እየመጡ\" እንደሆነ ተደርጎ ነው፡፡ ይህ ዘይቤ በኤርምያስ 7፡32 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"እኔ በመጪው ጊዜ… እሰራለሁ\" ወይም \"እኔ የምሰራበት…ጊዜ ይኖራል\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ የያህዌ አዋጅ/ትዕዛዝ ነው",
"body": "ያህዌ ስለ ራሱ በስሙ የሚናገረው/የሚምለው የተናገረው ነገር እርግጠኛ መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"ያህዌ ያዘዘው ይህንን ነው\" ወይም \"እኔ ያህዌ ያዘዝኩት ይህንን ነው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የእስራኤል ቤት",
"body": "\"ቤት\" የሚለው ቃል በቤት ውስጥ ለሚኖሩ ቤተሰቦች ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ይህ የሚያመለክተው የእስራኤልን መንግሥት ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 3፡18 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"እስራኤል\" ወይም \"የእስራኤል መንግሥት\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የይሁዳ ቤት",
"body": "\"ቤት\" የሚለው ቃል በቤት ውስጥ ለሚኖሩ ቤተሰቦች ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ይህ የሚያመለክተው፣ የይሁዳን እና የብንያምን ትውልድ የሚያጠቃልለውን የይሁዳን መንግሥት ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 3፡18 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"ይሁዳ\" ወይም \"የይሁዳ መንግሥት\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በእነዚያ ቀናት ወይም በዚያን ጊዜ",
"body": "\"በዚያን ጊዜ\" የሚለው ሀረግ ተመሳሳይ ትርጉም ሲኖረው \"በእነዚያ ቀናት\" የሚለውን ሀረግ ያጠናክራል፡፡ \"በእነዚያው በራሳቸው ቀናት\" ወይም \"በዚያኑ በራሱ ጊዜ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ለዳዊት የጽድቅ ቅርንጫፍ እንዲበቅል አደርጋለሁ",
"body": "ያህዌ የዳዊትን ትውልድ የሚገልጸው የዛፍ ግንድ ቅርንጫፍ እንደሆነ አድርጎ ነው፡፡ \"እኔ ጻድቅን ሰው ከዳዊት እንዲመጣ እና ለዳዊት ዘር ክብር እንዲያመጣ አደርጋለሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ምድሪቱ",
"body": "የእስራኤል ህዝብ፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይሁዳ… እየሩሳሌም",
"body": "እነዚህ ሁለት የከተሞች ስሞች በእነዚያ ከተሞች ለሚኖሩ ሰዎች ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ናቸው፡፡ \"የይሁዳ ሰዎች… የእየሩሳሌም ሰዎች\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይሁዳ ይድናል",
"body": "ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ \"እኔ ይሁዳን አድነዋለሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እየሩሳሌም በደህንነት/በሰላም ትኖራለች",
"body": "\"የእየሩሳሌም ሰዎች ከጠላቶቻቸው የተጠበቁ ይሆናሉ\""
},
{
"title": "እርሷ የምትጠራበት ይህ ይሆናል",
"body": "ያህዌ ስለ እየሩሳሌም ከተማይቱ ሴት እንደሆነች አድርጎ ይናገራል፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ \"እርሷን የሚሯት እንዲህ ብለው ነው\" ወይም \"እኔ ከተማይቱን የምጠራት እንዲህ ብዬ ነው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)"
}
]