am_jer_tn/33/04.txt

18 lines
2.0 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ከወውጊያ እና ከሰይፍ የተነሳ ከፈራረሱት ",
"body": "ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ሰዎቹ ከለዳውያንን ለመከላከያ ቅጥር ለመገንባት ቤቶችን አፈረሱ፡፡ \"ከውጊያ እና ሰይፍ ራሳቸውን ለመከላከል ሰዎች የከተማዋን ቤቶችን አፈራረሱ\" ወይም 2) \"ጦርነት ለማድረግ ሲሉ በጦርነት ከበባ አመጽ ለማነሳሳት ከለዳውያን ያፈራረሷቸው ቤቶች\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "ሰይፍ",
"body": "ይህ ወታደሮች በሰይፍ ሲገድሉ ለሰዎች በጥቃት መገደል ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በቁጣዬ እና በመአቴ",
"body": "\"ቁጣ\" እና \"መአት\" የሚሉት ቃላት በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም ሲኖራቸው የቁጣውን ታላቅነት ያጎላሉ፡፡ \"ከመጠን በላይ በሆነው ቁጣዬ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ፊቴን እሰውራለሁ/እደብለሁ",
"body": "ያህዌ በ\"ፊቱ\" ተወክሏል፡፡ ይህ ሀረግ የሚያሳየው የያህዌን በከተማይቱ ደስ አለመሰኘት ነው፡፡ \"እኔ ከእናንተ ዞር ብያለሁ\" ወይም \"ከእንግዲህ ለእናንተ ጥበቀ አላደርግም/እተዋችኋለሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]