am_jer_tn/32/24.txt

34 lines
2.9 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡",
"body": "ኤርምያስ ወደ ያህዌ መጸለዩን ቀጥሏል፡፡ "
},
{
"title": "የአፈር ቁልሉ እርሷን ለመያዝ እስከ ከተማይቱ ደርሷል",
"body": "የአፈሩ ቁልል እና ጠላት በላያቸው ቆሞ ሊያጠቃት በከተማይቱ ዙሪያ ገነባው፣ የተገለጸው አጥቂዎቹ ራሳቸው ከተማይቱን ለመውረር እንደ ደረሱ ተደርጎ ነው፡፡ \"ጠላት ያበጀው አፈር ቁልል፣ ጠላት ሊይዛት እስከሚያስችለው ለከተማይቱ እጅግ ቅርብ ነው\" (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "ከሰይፍ የተነሳ",
"body": "\"ሰይፍ\" የሚለው ቃል ወታደሮች ሰይፍ በሚጠቀሙበት፣ ለጦርነት ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ \"ምክንያቱም ወታደሮች ጥቃት ያደርሳሉ\" (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "ረሃብ፣ እና መቅሰፍት",
"body": "እነዚህ ረቂቅ ስሞች በግሳዊ ሀረግ ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ \"ህዝቡ የሚመገበው ምግብ የለውም፣ ደግሞም እያንዳንዱ ሰው ከህመም የተነሳ ደካማ ሆኗል\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "ከተማይቱ ለከለዳውያን እጅ ተላልፋ ተሰጥታ ነበር",
"body": "እዚህ ስፍራ \"እጅ\" ማለት ሀይል ወይም መቆጣጠር ማለት ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ \"አንተ እየሩሳሌምን ለከለዳውያን ወታደሮች አሳልፈህ ሰጥተሃታል\" (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "ይህ ይሆናል፣ አንተ ታያለህ",
"body": "\"አንተ በግልጽ እንደምታየው፣ ይህ ይሆናል\""
},
{
"title": "ምስክሮች ይህን መስክረዋል",
"body": "\"አንተ መሬን ስትገዛ ሰዎች ተመልክተዋል፣ ስለዚህም እነርሱ ለሌሎች ሰዎች አንተ መሬቱን እንደገዛህ መናገር/መመስከር ይችላሉ\""
},
{
"title": "ከተማይቱ ተሰጥታለች",
"body": "ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ \"እኔ ይህችን ከተማ ልሰጣት ነው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]