am_jer_tn/32/03.txt

38 lines
4.6 KiB
Plaintext

[
{
"title": "የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ እርሱን አስሮት ነበር",
"body": "ሴዴቅያስ ይህንን እንዲያደርግ ሌሎች ሰዎች ረድተውት እንደነበረ አንባቢው ይረዳ ዘንድ መተረጎሙ ይመረጣል፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እርሱን አስሮት ነበር",
"body": "አዚህ ስፍራ \"እርሱን\" የሚለው የሚያመለክተው ኤርምያስን ነው፡፡ እዚህ ስፍራ ኤርምያስ ለምን ራሱን በስም እንደሚጠቅስ ግልጽ አይደለም፡፡ በዩዲቢ ውስጥ እንደሚገኘው የመጀመሪያ መደብ በመጠቀም መተርጎም ትችላላችሁ፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ለምን እንዲህ ብለህ፣ ትንቢት ተናገራለህ",
"body": "ሴዴቅያስ ጥያቄውን የሚጠቀምበት ኤርምያስን ለመገሰጽ ነው፡፡ \"ትንቢት መናገርህን መቀጠልህ ስህተት ነው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህችን ከተማ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾር እጅ አሳልፌ ልሰጣት ነው",
"body": "ያህዌ ስለ ከተማይቱ፣ አንድ ሰው ለሌላው ሊያቀብለው እንደሚችለው ትንሽ እቃ አድርጎ ይናገራል፡፡ \"እጅ\" የሚለው ቃል እጅ ለሚሰራው ስራ ሀይል ወይም ቁጥጥር ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት / ነው፡፡ \"ይህችን ከተማ በባቢሎን ንጉሥ ቁጥጥር ስር ላደርጋት ነው\" ወይም \" የባቢሎን ንጉሥ በዚህች ከተማ ላይ ያሻውን እንዲፈጽም ልፈቅድለት ተነስቻለሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር ወይም ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እርሱ ይማርካታል",
"body": "አንባቢው የባቢሎን ንጉሥ ከተማይቱን እንዲቆጣጠር ሌሎች ሰዎች እንደረዱት ይገነዘብ ዘንድ መተርጎሙ ይመረጣል፡፡"
},
{
"title": "ለእርግጥ ለባቢሎን ንጉሥ እጅ ተላልፎ ይሰጣል",
"body": "\"እጅ\" የሚለው ቃል ለሀይል ወይም እጅ የሚሰራውን ለመቆጣጠር ሜቶኖሚ/ ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ \"እኔ በእርግጥ በባቢሎን ንጉሥ ቁጥጥር ስር አደርገዋለሁ\" ወይም \"እኔ በእርግጥ የባቢሎን ንጉሥ በእርሱ ላይ ያሻውን እንዲፈጽም እፈቅዳለሁ\" (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ከንጉሡ ጋር አፍ ለአፍ ይናገራል፣ ደግሞም ዐይኖቹ የንጉሡን ዐይን ይመለከታሉ",
"body": "እዚህ ስፍራ \"አፍ\" እና \"ዐይን\" የሚወክሉት መላውን ሰውነት ነው፡፡ \"ሴዴቅያስ ራሱ ንጉሥ ናቡከደነጾርን ይመለከተዋል በቀጥታም ከእርሱ ጋር ይነጋገራል\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ የያህዌ አዋጅ/ትዕዛዝ ነው",
"body": "ያህዌ ስለ ራሱ በስሙ የሚናገረው/የሚምለው የተናገረው ነገር እርግጠኛ መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"ያህዌ ያዘዘው ይህንን ነው\" ወይም \"እኔ ያህዌ ያዘዝኩት ይህንን ነው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እናንተ ትዋጋላችሁ",
"body": "እዚህ ስፍራ \"እናንተ\" የሚለው ብዙ ቁጥር ነው፡፡ (አንተ የሚለው ተውላጠ ስም መልኮች የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]