am_jer_tn/31/33.txt

18 lines
2.5 KiB
Plaintext

[
{
"title": "የእስራኤል ቤት",
"body": "\"ቤት\" የሚለው ቃል በቤት ውስጥ ለሚኖሩ ቤተሰቦች ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ይህ የሚያመለክተው የእስራኤልን መንግሥት ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 3፡18 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"እስራኤል\" ወይም \"የእስራኤል መንግሥት\" ወይም \"የእስራኤል ህዝብ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ የያህዌ አዋጅ/ትዕዛዝ ነው",
"body": "ያህዌ ስለ ራሱ በስሙ የሚናገረው/የሚምለው የተናገረው ነገር እርግጠኛ መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"ያህዌ ያዘዘው ይህንን ነው\" ወይም \"እኔ ያህዌ ያዘዝኩት ይህንን ነው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ህጌን በእነርሱ መሃል አደርጋለሁ፣ ደግሞም በልባቸው ላይ እጽፈዋለሁ",
"body": "እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም ሲኖራቸው፣ የያህዌ ህግ የእነርሱ አንድ ክፍል እንጂ በድንጋይ ላይ ተጽፎ የተቀመጠ ብቻ አለመሆኑን ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ እዚህ ስፍራ \"ልብ\" የሚወክለው \"ስሜትን\" ወይም \"ሀሳብን/አእምሮን\" ነው፡፡ \"ህጌ የሃሳባቸው እና ስሜታቸው ክፍል ይሆናል\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ከእነርሱ ከታናናሾቹ ጀምሮ እስከ ታላላቆቹ ድረስ",
"body": "ይህ ሀረግ ከታናሹ እስከ ታላላቆች ድረስ እያንዳንዱን ሰው ያመለክታል፡፡ \"አንድም ሳይቀር እያንዳንዳቸውን\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ከአጽናፍ አጽናፍ/ከዳር እስከ ዳር የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]