am_jer_tn/31/18.txt

34 lines
4.0 KiB
Plaintext

[
{
"title": "በእርግጥ የኤፍሬምን ሀዘን ሰምቻለሁ",
"body": "ኤፍሬም በእስራኤል የነበረው ትልቅ ነገድ አባት ነበር፡፡ የእርሱ ስም ለእስራኤል ህዝብ ሜቶኖሚ/ ነው፡፡ \"እኔ በእርግጥ የኤፍሬምን ትውልዶች ሀዘን ሰምቻለሁ\" ወይም \"እኔ በእርግጥ የእስራኤልን ህዝብ ሀዘን ሰምቻለሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አንተ ቀጣኸኝ፣ እኔም ተቀጣሁ",
"body": "ተናጋሪው ሀረጉን የሚደግመው፣ አንድም ያህዌ እርሱን እጅግ እንደቀጣው ለማሳየት ወይም ያህዌ እርሱን በቅጣት ሊያስተምረው የፈለገውን ማወቁን/መረዳቱን ለመናገር ነው፡፡ \"እኔ ተቀጣሁ\" የሚለው ቃል በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ \"አንተ እኔን ቀጣኸኝ፡፡ አዎን፣ አንተ እኔን ክፉኛ ቀጣኸኝ\" ወይም \"አንተ ቀጣኸኝ፣ እኔም ከአንተ የተማርኩት ስትቀጣኝ ነው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እንዳልተገራ ወይፈን ተቀጣሁ",
"body": "ሰዎች ወይፈን ሲገሩ፣ ይገርፏቸዋል፣ ካልሆነ እንዲጨነቁ ያደርጋሉ፡፡ ያህዌ የእስራኤልን ህዝብ እንዲጨነቅ አድርጓል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "መቅጣት",
"body": "ሌላው አማራጭ ትረጉም \"ስርአት ማስያዝ\" ነው"
},
{
"title": "ጭኔን ጻፍሁ/ጭኔን በእጄ መታቱ",
"body": "በሀዘን፡፡ በእናንተ ቋንቋ ሰዎች ማዘናቸውን ለመግለጽ የተለየ ሀረግ ወይም ድርጊት የሚጠቀሙ ከሆነ እዚህ ስፍራ ያንን ተክታችሁ መጠቀም ትችላላችሁ፡፡ \"ግንባሬን ፈተግሁ\" በሚለውውጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ትምዕርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እኔ አፈርኩ ተዋረድኩም",
"body": "\"ሀፍረት\" እና \"ውርደት\" የሚሉት ቃላት በመረቱ ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆኑ ሀፍረት የሚለውን ሀሳብ ያጎላሉ፡፡ \"እኔ ሙሉ ለሙሉ አፍሬ ነበር\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ኤፍሬም የእኔ ውድ ልጄ አይደለምን? እርሱ ለእኔ ውድ አይደለምን፣ አስደሳች ልጄ አይደለምን?",
"body": "ያህዌ ህዝቡን ለማጽናናት እየሞከረ በማባባት ይናገራል፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች በዐረፍተ ነገር መልክ ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ \"ኤፍሬም ወድ ልጄ ነው፡፡ እርሱ የእኔ ውድ ነው፣ ደስ የምሰኝበት ልጄ ነው፡፡ በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ የያህዌ አዋጅ/ትዕዛዝ ነው",
"body": "ያህዌ ስለ ራሱ በስሙ የሚናገረው/የሚምለው የተናገረው ነገር እርግጠኛ መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"ያህዌ ያዘዘው ይህንን ነው\" ወይም \"እኔ ያህዌ ያዘዝኩት ይህንን ነው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]