am_jer_tn/31/10.txt

22 lines
2.1 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡",
"body": "ያህዌ እንዴት የእስራኤልን ህዝብ ከተማረኩበት ከባቢሎን እንደሚመልስ መናገሩን ቀጥሏል፡፡"
},
{
"title": "አድምጡ … ተናገሩ",
"body": "ያህዌ ለአገራት ይናገራል፣ ስለዚህ እነዚህ ግሶች ብዙ ቁጥር ናቸው፡፡ (ተውላጠ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እስራኤልን የበተናት እርሱ መልሶ ይሰበስባታል ደግሞም ይተብቃታል",
"body": "ያህዌ ስለ ራሱ እንደ ሌላ አድርጎ ይናገራል፤ ስለ እስራኤል ህዝብ ደግሞ እርዳታ ያጣች ሴት አድርጎ ይናገራል፡፡ \"እኔ ህዝቤ እስራኤል በአገራት መሃል እንዲበተን አድርጌያለሁ፣ ነገር ግን አሁን ወደ ቤታቸው እመልሳቸዋለሁ ደግሞም እጠብቃቸዋለሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተውላጠ ስሞች እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እረኛ በጎቹን እንደሚጠብቅ ",
"body": "እረኛ በጎቹን ይጠብቃል ይንከባከባልም፣ እናም ያህዌ እስራኤላውያንን እንደሚንከባከብ እና እንደሚጠብቅ ቃል እየገባ ነው፡፡\" (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ያህዌ ያዕቆብን እንደ ተቤዠ ለእርሱ እጅግ ከባድ ከሆነበት እጅ እንዳዳነው",
"body": "እነዚህ ሁለት ሀረጎች በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም ሲኖራቸው፣ የእስራኤልን ህዝብ የታደገው ያህዌ እንደሆነ ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ \"ያህዌ የእስራኤልን ህዝብ እጅግ ከባድ ከሆኑባቸው \"ጠላቶቻቸው ታድጓል በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)"
}
]