am_jer_tn/31/01.txt

34 lines
2.9 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡",
"body": "ኤርምያስ ብዙውን ጊዜ ትንቢቱን የሚጽፈው በግጥም መልክ ነው፡፡ የዕብራውያን ስነግጥም የተለያዩ ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤዎችን ይጠቀማል፡፡ (ስነግጥም እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በዚያን ጊዜ",
"body": "ይህ የሚያመለክተው እግዚአብሔር ክፉዎችን የሚቀጣበትን ጊዜ ነው፡፡ "
},
{
"title": "ይህ የያህዌ አዋጅ/ትዕዛዝ ነው",
"body": "ያህዌ ስለ ራሱ በስሙ የሚናገረው/የሚምለው የተናገረው ነገር እርግጠኛ መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"ያህዌ ያዘዘው ይህንን ነው\" ወይም \"እኔ ያህዌ ያዘዝኩት ይህንን ነው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ከሰይፍ የተረፉት በበረሃ ሞገስ ያገኛሉ",
"body": "\"ሞገስ ማግኘት\" የሚለው ሀረግ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ \"ከሰይፍ ላመለጡ ሰዎች እኔ በበረሃ ስፍራ ጸጋን በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ከሰይፍ ያመለጡ",
"body": "\"ሰይፍ\" የሚለው ቃል ጦርነት ለሚለው ሜቶኖሚ/ ነው፡፡ \"ከጦርነት ያመለጡ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በበረሃ ለእስራኤል እረፍት ለመስጠት እወጣለሁ",
"body": "ሊሰጥ የሚችለው አማራጭ ትርጉም \"እስራኤል ረፍት ለማግኘት ወደ በረሃ ይወጣል\""
},
{
"title": "ያህዌ ለእኔ ተገለጠልኝ",
"body": "ኤርምያስ ስለ እራሱ፣ እርሱ የእስራኤል ህዝብ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በቃል ኪዳን ታማኝነት እኔ አንቺን ወደ ራሴ ሳብኩሽ",
"body": "\"ታማኝነት\" የሚለው ረቂቅ ስም \"ታማኝ\" ወይም \"በታማኝነት\" ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ \"እኔ ለቃል ኪዳኔ ታማኝ ሆኜ ወደ ራሴ አቀረብኩሽ\" ወይም \"እኔ በታማኝነት ወድጄ ወደ ራሴ አቀረብኩሽ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ) "
}
]