am_jer_tn/29/22.txt

18 lines
2.3 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ስለ እነዚህ ሰዎች መረገም በባቢሎን በተማረኩ አይሁዶች ዘንድ ሁሉ ይወራል",
"body": "ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ \"በባቢሎን የሚገኙ የይሁዳ ምርኮኞች ስለ እነዚህ ሰዎች መረገም ይናገራሉ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የተጠበሰ",
"body": "ይህ ቃል ብዙውን ጊዜ ምግብን ሙሉ በሙሉ ማቃጠልን ሳይሆን፣ በሚነድ እሳት ላይ ወይም በመጥበሻ ከሚገባው በላይ ማብሰልን ያመለክታል፡፡ ለዚህ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ይህ ዩፊምዝም/የማያስደስትን ቃል ሻልባለ ቃል መተካት/ ነው፡፡ \"እስከ ሞት መቃጠል\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ ወይም 2) የንጉሡ ወታደሮች እሳቱ ቀስ በቀስ ጠብሶ እስከሚገድላቸው ድረስ በምሰሶ ላይ አስረው ወደ እሳቱ አቅረበው ይለበልቧቸዋል፣ ነገር ግን አካላቸውን ሙሉ ለሙሉ እንዳያቃጥለው ከእሳቱ ራቅ ያደረጓቸዋል፡፡ (ዩፊምዝም/የማያስደስትን ቃል ሻልባለ ቃል መተካት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እኔ አውቃለሁ፣ እኔ ምስክር ነኝ",
"body": "እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፣ ያህዌ የሚደጋግማቸው ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ የያህዌ አዋጅ/ትዕዛዝ ነው",
"body": "ያህዌ ስለ ራሱ በስሙ የሚናገረው/የሚምለው የተናገረው ነገር እርግጠኛ መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"ያህዌ ያዘዘው ይህንን ነው\" ወይም \"እኔ ያህዌ ያዘዝኩት ይህንን ነው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]