am_jer_tn/29/12.txt

38 lines
3.0 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡",
"body": "ያህዌ ምርኮኛ በሆኑ እስራኤላውያን ላይ ምን እንደሚደርስ መናገሩን ቀጥሏል"
},
{
"title": "ወደ እኔ ትጣራላችሁ",
"body": "ጸሎት የተገለጸው በከፍተኛ ድምጽ እንደመጣራት ተደርጎ ነው"
},
{
"title": "እኔም እሰማችኋለሁ",
"body": "ይህ የሚያመለክተው ያህዌ እነርሱ የሚፈልጉትን እንደሚሰጣቸው ነው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እናንተ ትፈልጉኛላችሁ",
"body": "ያህዌ የሚጠይቀውን ለማወቅ መፈለግ የተገለጸው ያህዌ የት እንዳለ ለማግኘት እንደ መሞከር ተደርጎ ነው፡፡ \"እኔ እንድታደርጉ የምጠይቀውን፣ እናንተ ለማድረግ ትፈልጋላችሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እናንተ በሙሉ ልባችሁ እኔን ትፈልጋላችሁ",
"body": "\"እናንተ እኔን የምትፈልጉት ሙሉ ለሙሉ በቅንነት ይሆናል\""
},
{
"title": "ለእናንተ እገኛለሁ",
"body": "ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ \"እኔን እንድትፈልጉኝ እፈቅድላችኋለሁ\" ወይም \"እኔን ማግኘት ትችላላችሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመለከቱ)"
},
{
"title": "ይህ የያህዌ አዋጅ/ትዕዛዝ ነው",
"body": "ያህዌ ስለ ራሱ በስሙ የሚናገረው/የሚምለው የተናገረው ነገር እርግጠኛ መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"ያህዌ ያዘዘው ይህንን ነው\" ወይም \"እኔ ያህዌ ያዘዝኩት ይህንን ነው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እድል ፈንታችሁን ዳግም እመልሳለሁ",
"body": "\"ነገሮች ዳግም ለእናንተ መልካም እንዲሆኑ አደርጋለሁ\" ወይም \"ዳግም መልካም ህይወት እንድትኖሩ አደርጋለሁ\""
},
{
"title": "እንድትሰደዱ አደርጋለሁ",
"body": "ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ \"ወደ ስደት እልካችኋለሁ\" ወይም \"ስደተኞች እንደትሆኑ አደርጋለሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመለከቱ)"
}
]