am_jer_tn/28/12.txt

18 lines
2.1 KiB
Plaintext

[
{
"title": "የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፣ \"ሂድ",
"body": "\"ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር የዋለው ከእግዚአብሔር ዘንድ ልዩ መልዕክትን ለማስተዋወቅ ነው፡፡ ተመሳሳይ የሆነው ሀረግ በኤርምያስ 1፡4 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"ያህዌ ለኤርምያስ መልዕክት ሰጠው፡፡ እንዲህም አለው፣ ‘ሂድ\" ወይም \"ያህዌ ይህንን መልዕክት ለኤርምያስ ነገረው፡ 'ሂድ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "አንተ የእንጨቱን ቀንበር ሰብረሃል፣ ነገር ግን እኔ በምትኩ የብረት ቀንበር አደርጋለሁ",
"body": "\"አንተ ደካማውን ቀንበር ሰበርክ ነገር ግን እኔ ይህንን አንተ ልትሰብረው በማትችለው ቀንበር እተካለሁ\""
},
{
"title": "የሰራዊት ጌታ ያህዌ… እንዲህ ይላል",
"body": "ኤርምያስ ብዙውን ጊዜ እነዚህን ቃላት የሚጠቀመው ከያህዌ ዘንድ ጠቃሚ መልዕክትን ለማስተዋወቅ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 6፡6 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡"
},
{
"title": "ናቡከደነጾርን እንዲያገለግሉት በእነዚህ ሁሉ አገራት አንገት ላይ የብረት ቀንበር አድርጌያለሁ",
"body": "ያህዌ አገራትን የናቡከደነጾር ባሪያዎች እንደሚያደርግ የሚናገረው ከባድ ስራ እንዲሰሩ በበሬዎች ላይ ቀንበር እንደሚጭንባቸው አይነት አድርጎ ነው፡፡ \"እኔ እነዚህን ሁሉ አገራት ባሮች አድርጌያለሁ፣ እናም እነርሱ ናቡከደነጾርን ማገልገል ይኖርባቸዋል\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ) "
}
]