am_jer_tn/27/14.txt

26 lines
2.2 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡",
"body": "ያህዌ በኤርምያስ በኩል ለይሁዳ ንጉሥ እና ህዝብ መናገሩን ቀጥሏል፡፡"
},
{
"title": "ቃሎቻቸውን አትስሙ",
"body": "ያህዌ ህዝቡን ስለ ሀሰተኛ ነቢያት እርሱ እንዳልላካቸው እና እየዋሽዋቸው እንደሆነ ያስጠነቅቃል፡፡"
},
{
"title": "እኔ ወደ እናንተ አልላኳቸውም",
"body": "\"እኔ እነርሱን ስላልላኳቸው\""
},
{
"title": "ይህ የያህዌ አዋጅ/ትዕዛዝ ነው",
"body": "ያህዌ ስለ ራሱ በስሙ የሚናገረው/የሚምለው የተናገረው ነገር እርግጠኛ መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"ያህዌ ያዘዘው ይህንን ነው\" ወይም \"እኔ ያህዌ ያዘዝኩት ይህንን ነው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በስሜ ሀሰትን ይተነብያሉ",
"body": "\"በስሜ\" የሚለው ሀረግ የሚወክለው በያህዌ ሀይል እና ስልጣን ወይም የእርሱ ወኪል ሆኖ መናገርን ነው፡፡ እዚህ ስፍራ እነዚህ ነቢያት መልዕክታቸውን ከያህዌ እንደተቀበሉ ይናገራሉ፣ ነገር ግን ከእርሱ አልተቀበሉም፡፡ \"ሀሰት/ማታለል\" የሚለው ረቂቅ ስም \"ያታልላሉ\" በሚል ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ \"በሀሰት ተንቢት ሲናገሩ ከእኔ ተቀብለው እንደሚናገሩ ወራሉ፣ ሆኖም ግን እያታለሏችሁ ነው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ረቂቅ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እኔ አባርራችኋለሁ",
"body": "\"እኔ አገራችሁን ለቃችሁ እንድትወጡ አስገድዳችኋለሁ\""
}
]