am_jer_tn/26/18.txt

38 lines
4.2 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡",
"body": "ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ"
},
{
"title": "ሞሬታዊ",
"body": "ከሞሬት ከተማ ወይም አካባቢ የሆነ/የመጣ ሰው"
},
{
"title": "የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል",
"body": "ኤርምያስ ብዙውን ጊዜ እነዚህን ቃላት የሚጠቀመው ከያህዌ ዘንድ ጠቃሚ መልዕክትን ለማስተዋወቅ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 6፡6 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡"
},
{
"title": "ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች…የቤተ መቅደሱ ተራራ ዳዋ የወረሰው ኮረብታ ይሆናል",
"body": "\"ጽዮን \" እና \"የቤተ መቅደሱ ኮረብታ\" የሚሉት የሚያመለክቱት አንድን ስፍራ ነው፡፡ ገበሬ መሬቱን ሲያርስ አፈሩን ይገለብጣል፣ በእርሻው ውስጥ የሚገኙ ቅጠላ ቅጠሎች ሁሉ ይነቃቅላል፡፡ ቁጥቋጦ ማንም ለምንም የማይፈልጋቸውን አረሞች የያዘ ነው፡፡ እነዚህ ሁለት ዘይቤዎች በተመሳሳይ ጊዜ ቃል በቃል እውነተ ተደርገው አይወሰዱም፣ ነገር ግን ይህ አገላለጽ ያህዌ ወራሪዎች የቤተ መቅደሱን አካባቢ ሙሉ ለሙሉ መደምሰስ እንዲችሉ እንደሚፈቅድላቸው በትኩረት ይገልጻል፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሕዝቅያስ… ለሞት ተሰጠን?",
"body": "ተናጋሪዎቹ አድማጮቻቸው እነርሱ የሚናገሩትን እንዲሰሟቸው እየሞከሩ ነው፡፡ \"ሕዝቅያስ ራሱን ለሞት አሳልፎ እንዳልሰጠ… እናተ ራሳችሁ በሚገባ ታውቃላችሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "መላው ይሁዳ",
"body": "ምድሪቱ የሚለው ለመላው በዚያ ለሚኖረው ህዝብ ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ \"መላው የይሁዳ ህዝብ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እነርሱ…እርሱስ ያህዌን አልፈራምን፣ ደግሞስ የያህዌን ፊት በትህትና አልፈለገምን?",
"body": "ተናጋሪዎቹ አድማጮቻቸው እነርሱ የሚናገሩትን እንዲሰሟቸው እየሞከሩ ነው፡፡ \"እነርሱ…ሕዝቅያስ ራሱን ለሞት አሳልፎ እንዳልሰጠው እናተ ራሳችሁ በሚገባ ታውቃላችሁ ስለዚህም ያህዌ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የያህዌን ፊት በትህትና ፈለገ",
"body": "ፊት የሚለው መላ ሰውነትን የሚገልጽ ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ \"የያህዌ ቁጣ እንዲበርድ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እኛ በገዛ ህይወታችን ላይ የባሰ ጥፋት እንፈጽማለን?",
"body": "ተናጋሪዎቹ አድማጮቻቸው እነርሱ ከሚናገሩት ጋር እንዲስማሙ ለማድረግ እየሞከሩ ነው፡፡ \"ህይወታችን\" የሚለው ቃል ለሰዎቹ ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ \"ኤርምያስን ብንገድለው፣ በራሳችን ህይወት ላይ የከፋ ክፉ ነገር እንፈጽማለን\" ወይም \"በራሳችን ላይ የከፋ ነገር ማድረግ አንፈልግም\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]